1. የከተማ አስተዳደሩ መሬትን ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ለልማት ለማዋል 89 የሚሆኑ ቦታዎችን ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቅይጥ አገልግሎት እንዲውል የከተማውን ፕላን ባስጠበቀ አግባብ በግልፅ ጨረታ እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
2. በከተማችን ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው ቤት የሚገነቡበትን አሰራር ለመወሰን በተዘጋጀ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን በዚሁ አግባብ በከተማችን የሚኖሩና የቤት ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ችግር በሚቀርፍ አግባብ የከተማ አስተዳደሩ መሬት፣ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች ዲዛይን፣ ማህበራቱን የማደራጀትና ግንባታው በሚጀመርበት ጊዜ የመቆጣጠር ሀላፊነት የሚወስድ ሆኖ በማህበር ተደራጅተው የጋራ ህንጻ የሚገነቡ ሰራተኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች የፀጥታ አካላት ከተደራጁ በኋላ ቁጣባ በአግባቡ መቆጠብ የሚችሉና አስተዳደሩ በሚያዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ከፍታቸውን የጠበቁ ህንፃዎች ለመገንባት ዝግጁ የሆኑ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ማድረግ የሚያስችል ደንብ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደቱ በከተማችን ካለው የቤት አቅርቦት ማህቀፍ ጋር ተጣጥሞ እንዲፈፀም ውሳኔ አሳልፏል፡፡
3. ካቢኔው በቀጣይ የተወያየበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ደህንነትን ቀድመን ለመከላከል በሚያስችል ደንብ ላይ ሲሆን በዚህም በከተማችን ለአደጋ ስጋት የሆኑ የህንፃ ዲዛይን ማስተካከያዎች፣ በግንባታ ላይ ያሉ ህንፃዎች ሊያሟሏቸው የሚገባ የደህንነት ጥንቃቄዎች፣ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አጠቃቀም ሁኔታና ለቅድመ መከላከልም ሆነ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የአደጋ መውጫ አስፈላጊውን የህንፃ ዲዛይን ማስተካከያ እንዲያደርግ እንዲሁም በከተማችን የማዕድን ማውጣት ሂደት ላይ ሊሟሉ የሚገባቸው የቅድመና የአደጋ መከላከያ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በከተማችን በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን አደጋ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ደንብ በመሆኑ አስፈላጊውን የአፈፃፀም ሂደት ባሟላ መልኩ ወደ ተግባር እንዲገባ ደንቡን አፅድቋል፡፡
4. የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ እስካሁን ድረስ 1 ቢሊዬን ብር መድቦ የተለያዩ ምርቶች ወደ ከተማዋ እንዲገቡ የተደረገ ቢሆንም አሁንም የዘይት አቅርቦት ላይ ያለ እጥረት መኖሩን ካቢኔው አፅንኦት ሰጥቶ ከተወያየ በኋላ ለዘይት አቅርቦት ብድር የሚሆን 400 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ድጎማ መድቧል፡፡