የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ከሃምሌ 2014 ጀምሮ በኮተቤ የትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲጠና በቆየው የብዝሃ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን ለመወሰን በተደረገው ጥናት ላይ ዝርዝር ውይይት አድርጓል፡፡
ለቀጣይም ከዘርፉ ባለሙያዎች ፤ ከባለድርሻና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበትና ተጨማሪ ግብዓት ተወስዶበት የብዝሃ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርቱ ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አቅጣጫ ሰጥቶበታል፡፡