የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 2ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች
ካቢኔው በሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማውን ልማት ለማፋጠን የነዋሪውን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ፣ ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ፣ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ጥያቄ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
1. የመኖሪያ ቤቶችን በመንግስትና የግል አጋርነት በ70/30 አሰራር መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀውን 35 ሄክታር መሬት ላይ ተወያይቶ ወስኗል።
2. ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የስራ እድል የሚፈጥሩ የ373 ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ
እነሱም ፦
2.1. ለኢንዱስትሪ ልማት
2.2 ሆቴሎችና ሞሎች ፣
2.3 የሀይማኖት ተቋማት ፣
2.4 ቀደም ሲል በካቢኔ ተወስነው የመሬት ለውጥ የቀረበባቸው ቦታዎች ፣ ለተለያዩ የግንባታ ግባዓት ማስቀመጫ የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታዎች ናቸው።
3.ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ መረጋጋት የዋጋ መናር መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ምርት ወደ ከተማ እንዲገባና እንዲሰራጭ ግብረ ኃይል አቋቁሟል ።
4.ለተማሪዎች ምገባ የሚያቀርቡ እናቶች በአሁኑ ዋጋ ማቅረብ መቸገራቸውን መነሻ በማድረግ ለተማሪዎች ምገባ በወር 54,000,000 ብር (ሀምሳ አራት ሚሊየን) በዓመት 540,000,000 ብር (አምስት መቶ አርባ ሚሊየን) ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፤ ይህ ማለት ለአንድ ተማሪ በቀን ሃያ ብር የነበረው ወደ የሀያ ሶስት ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል ።
5.ከወቅቱ ዋጋ መናር እና የገበያ አለመረጋጋት ጋራ ተያይዞ የነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ እንዳይጨምሩ ተውስኗል።