1. ካቢኔው መጀመሪያ የተወያየው የኑሮ ውድነቱን ጫና ለመቀነስ እና ገበያውን ለማረጋጋት እንዲቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ሥራዎች ድርጅትን ለማቋቋም ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
2. በመቀጠል የዳግማዊ ሚኒሊክ የሕክምናና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደገና ለማቋቋም ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
3. የከተማ አስተዳደሩ መዋቅራዊ ፕላን የፀደቀበት አዋጅ ቁጥር 48/2009 በሚያዘው መሰረት ተጠንተው በቀረቡ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል::
እነዚህ የፕላን ማሻሻያዎች መዋቅራዊ ፕላን መነሻ በማድረግ የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) በማዘጋጀት በከተማዋ በተለዩ ቦታዎች የመንገድ ትስስርን (network)፣ ጥግግትን ፣ የከተማዋ የአረንጏዴ ልማት ቦታዎችን ማሻሻልን ፣ የህፃናት የመጫወቻ ቦታዎችን ማስፋፋትን እና የከተማዋን ውበት የሚጨምሩ ሌሎች ፕላኖችን ለማሻሻል በቀረበው ጥናት ላይ ተወያይቶ ጥናቱን ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ አፅድቋል ይህም ከተማዋን በፕላን እንድትመራ በማድረግ ጉልህ ሚና የሚጫወት ይሆናል::