የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይፋ ያደረጋቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች እውነታዎች፡-

ሁለቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች በጠቅላላው 7.6 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

የመጀመርያው የግብርና ምርት ማቅረቢያና መሸጫ ማእከል በ6 ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጪ በተለያዩ ሶስት ቦታዎች (በለሚ ኩራ ክ/ከተማ 2 ፕሮጀክትና ፤ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አንድ ፕሮጀክት) የሚገነቡ ይሆናል

ለሚ – ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 በ3.88 ሄክታር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 በ2.8 ሄክታር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 በ2.12 ሄክታር የሚያርፉ ናቸው።

ፕሮጀክቱ በከተማችን አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝና ገበያውን በማረጋጋት ለአምራቹም ለተጠቃሚውም ተመጣጣኝ ምርቶች እንዲቀርብ የሚያደርግ ነው፡፡

ኦቪድ ግሩፕ የተሰኘው ድርጅት በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የሚገነባው ፕሮጀክት ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የተካተቱ ነገሮችን በተመለከተ ፡- መደብሮች ፤ የጅምላ እና የችርቻሮ ገበያ አካባቢ፤ ሱፐርማርኬት፤ የቢሮ ብሎክ ለአስተዳደር፤ መጸዳጃ ቤቶች እና መገልገያዎች፤ የመግቢያ መንገድ እና የመኪና ማቆሚያ ፤ ዘመናዊ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ስርዓት ይዟል፡፡

የፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ጊዜ 6 ወራት ነው ።

ሁለተኛው በ1.5 ቢሊዮን በሆነ ወጪ የሚገነባው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፍያ የB+G+8 ፕሮጀክት ግንባታ ነው፡፡

ይህ ግንባታ በርካታ ገፅታዎች ያሉት ሲሆን – ለተኝቶ ታካሚ =200 አልጋዎች – ለድንገተኛ =27 ክፍሎች- 125 መጸዳጃ ቤቶች- የቀዶ ጥገና ማዕከል – አንድ የፊዚዮቴራፒ ማዕከል – የኢሜጂንግ ማዕከል – ላቦራቶሪ – – የልጆች እና ጎልማሶች ICU ማዕከል – የነርሲንግ ጣቢያ- የስብሰባ አዳራሽ ይኖሩታል፡፡

ተቋራጭ ዮሃንስ ሀይሌ ኮንትራክተር ሲሆን አማካሪ ሲጎር አማካሪ ነው።

የፕሮጀክት ቆይታ ደግሞ 18 ወራት የፕሮጀክት ወጪ 1.5 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው፡፡