👉 የቤት ልማትን በተመለከተ 37,990 የሚሆኑ ቤቶችን ለባለእድለኞች የተላለፈ ሲሆን ለቁልፍ ርክክብ ዝግጁ የሆኑ የጋራ መኖርያ ቤቶች 57,710 ማድረስ ተችሏል፡፡ የተቀሩትንም መሠረትዊ የሆኑትን ዋና ዋና ሥራዎች ለማጠናቀቅ ከንግድ ባንክ የቦንድ ብድር ተጠይቆበታል፡፡
👉 5ሺህ ባለ አራት እና አስር ወለል ተገጣጣሚ ቤቶች በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው እንዲጠናቀቁ ስራው ተጀምሯል፡፡
👉 የመሬት ልማት ስራ ለሙሰኞችና በአቋራጭ መበልፀግ ለሚፈለጉ ህገወጥ ሀይሎች የተጋለጠ ከመሆኑ የተነሳ ባለፉት 6 ወራት ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን ግብረሃይል በማቋቋም ችግሩን በማጥራት በውጤቱ ላይ ተመስርቶ የተጠያቂነት ስርአት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
👉 የመሬት ወረራ ለመቀልበስ በተሰራው ስራ ከ1ሺህ ሄክታር በላይ ማስመለስ ተችሏል፡፡ 383.3 ሄክታር መሬት በድጋሚ መብት በሌላቸው አካላት የተያዙ እንዲሁም ለአረንጓዴ ልማት ከተለዩ 252 ቦታዎች ውስጥ 35 ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸው ተረጋግጦ የእርምት እርምጃ በመውሰድ ወደ መሬት ባንክ እና መሬቱን ሲጠቀሙበት ለቆዩ ነባር አርሶ አደሮች እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
👉 በአጠቃላይ ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ ስፋት ያላቸው ቦታዎችና 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ከማድረግ ጎን ለጎን በህገወጥ መሬት ወረራ የተሳተፉ ከማዕከል እስከ ወረዳ 155 የሚሆኑ አመራሮችና 88 ባለሙያዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰዶባቸዋል፡፡
👉 የለማ መሬት ዝግጅትና አቅርቦት በተመለከተ፤ ለቤት ልማት፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ፣ ለምትክ ቦታ፣ ለሊዝ ጨረታ በድምሩ 130 ሄክታር ለማዘጋጀት ታቅዶ 103.2 ሄክታር መሬት ማዘጋጀት ተችሏል፡፡
👉 476 ሺህ የይዞታ ማህደራት ለማጥራትና ለማደራጀት ታቅዶ ከ444 ሺህ በላይ የይዞታ ማህደራት በማጣራት፣ ማጭበርበር የሚፀምባቸውን የቆዩ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ቲተሮች እንዲሁም ቀድሞ 471,056 የሚሆኑ ካርታዎችን በማስወገድ በአዲስ መልክ የመተካት ሥራ ተሰርቷል፡፡
👉 የህብረተሰብ ተሳትፎ በተመለከተ አመቱ 250 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ከ238 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ በተሰበሰበው ሃብትም 25 የአነስተኛ ድልድይ ግንባታ፤ 38 ኪሎ.ሜትር ሰብቤዝ፤ ከ25 ኪሎሜትር በላይ የኮብል የመንገድ ጥገና፤ 37 ኪሎሜትር ቱቦ ቀበራ እንዲሁም 58 የጋራ መፀዳጃ ቤቶች የተሰሩ ተሰርተዋል፡፡
👉 ከትራንስፖርት አቅርቦት አንፃር በከተማችን ካሉ11,044 የብዙሀንና ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል በየቀኑ ከ10ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች ወደ ስምሪት ገብተው አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፡፡ የአውቶብስ ግዢ የ110 አውቶብሶች ግዥ እየተከናወነ ነው፡፡
👉 ከመንገድ መሰረተ ልማት ስራችን አንጻር በግማሽ አመቱ በ6.05 በጀት 99 ኪሎ ሜትር ተገንብቷል፡፡
👉 የመንገድ ጥገና በተመለከተ፤ 565 ኪሎሜትር መጠገን ተችሏል፡፡
👉 የከተማችን የውሃ አቅርቦት 7.2. ቢሊዮን ብር ተመድቦ 87 ሚሊዮን ሜትርኩበ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፤ ከመንገድ መሰረተ ልማት አንጻር በ6.05 ቢሊዮን ብር 99 ኪሎ ሜትር ፤የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ስራችንን 120 ሄክታር ቦታዎችንና ፓርኮችን ማልማትና 11.4 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል፡፡
👉 በስፖርት ዘርፉ የተሰሩ መደበኛ ስራዎች እንደተጠበቁ ሆኖ፤ በተለያዩ አካባቢዎችና በስብዕና ማዕከላት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፖርት ለጤና ተሳትፎቸው እንዲጎለብት ተደርጓል፡፡