በተለይም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የነበረውን ብልሹ አሰራር :ሌብነትን ለማስተካከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ይረዳ ዘንድ የዘመናዊ የቢሮ ግንባታና የተቋማዊ ሪፎርምና የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመተግባር በክብርት ከንቲባ አስተባባሪነት የኢትዮ ቴሌኮም ፤የአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ፤የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ተቋማት የተሳተፉበት የዲጂታል አገልግት መስጠት የሚያስችል ስራ የፊታችን ቅዳሜ ለምረቃ የሚያበቃ ስራ በትጋት ተሰርቶ ነበር፡፡
ነገር ግን በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ የተዘጋጀው ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበት መሰረተ ልማቱ ወድሟል፡፡
የህዝቡ ፋይልና ዳታ እንዲሁም መረጃዎች ላይ ግን የደረሰ አደጋ የለም።
የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት ሲሆን ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል፡፡
የአካባቢው ማህበረሰብም መንግስት የጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
አሁንም የጀመርነውን የህዝባችን ጥያቄ የመመለስና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታት ጥረታችንን ማንም ምድራዊ ሀይል ሊያስቆመው አይችልም፡፡
ከህዝቡ ጋር ሆነን የከተማችን ብልፅግና እውን እናደርጋለን!!