የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ላሳዩት ኢትዮጲያዊ ጀግንነት እና ላስገኙት ውጤት የምስጋና መርሃ ግብር ነገ ያካሄዳል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደ 18ኛው ዓለም ዐቀፍ የአትሌቲክስ ሻምፕዮን ላይ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ልዑካን ቡድኑ ለማመስገን የተለያዩ ሽልማቶችን እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል ።
የከተማችን ነዋሪዎችም ነገ ማለዳ ምስጋናቸውን የሚገልፁበት ደማቅ ስነስርዓት ይካሄዳል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!