* ስምምነቱ የተገልጋዮችን እንግልት ይቀርፋል ተብሏል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ።
የመግባቢያ ስምምነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮን የገቢ አሰባሰብ ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የለማው ደራሽ የተቀናጀ ፕላትፎርም የገቢዎች ቢሮ የሚሰጠውን የግብር መሰብሰብ አገልግሎት ሥርዓት የሚያዘምን፣ የግብር ከፋዮችን እንግልት የሚያስቀር እንዲሁም የንግድ ተቋማት የዕርስ በርስ ግብይትና ሽያጭን በኦንላይን በማድረግ በየትኛውም ቦታ፣ በጊዜ ሳይገደቡና ሳይንገላቱ መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን ተገልጿል ፡፡