ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መቀሌ ከተማ በመገኘት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ለሆኑት ዶክተር ሙሉ ነጋ ድጋፉን አስረክበዋል ፡፡በቆይታቸውም ከክልሉ አስተዳደር አመራሮችና ከመቀሌ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግነው ድጋፍ ሲሆን አብሮነታችንን ፍቅራችንን እና ለህዝቡ ያለንን አክብሮት ለማሳየት ያደረግነው ነው ብለዋል።
ምክትል ከንቲባዋ መሪዎች ከግል ፍላጎታችን ወጣ ብለን ስለህዝባችን ልንኖር ይገባል ያሉ ሲሆን በክልሉ የተረጋጋ ሰላም እስኪሰፍንና አገልግሎት አሰጣጡ ወደነበረበት እስኪመለስ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡሀ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች ፣የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች በህግ ማስከበሩ ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በዓይደር ሆስፒታል በመሄድ ጠይቀዋል ።