የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል በመንግስትና የግል ሴክተሩ አጋርነት (public private partnership) የኩላሊት እጥበት ማእከል ማቋቋሙ የሚታወቅ ሲሆን አስተዳደሩ ከፍለው መታከም ለማይችሉ የኩላሊት እጥበት ማእከል ህንፃውን ከማመቻቸት ጀምሮ ሰራተኞችን በመቅጠር እንዲሁም የአብ ሜዲካል ማእከል ደግሞ የኩላሊት እጥበት ማሽኖቹን በማቅረብ እና ሌሎች ሙያዊ እገዛ በማድረግ በጋራ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በ2015 በጀት አመት ከፍለው የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ ዜጎች 20 ሚሊዮን ብር በመመደብ የኩላሊት እጥበት እንዲያከናውኑ ወጪውን መሸፈኑን በሆስፒታሉ በተካሄደው የአይን ህክምና ማእከል የምርቃት ስነስርዓት ላይ ይፋ ተደርጓል።