የ2014 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በይፋ ተጀመረ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለከተማ አዲስ ምዕራፍ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የ2014 የትምህርት ዘመን በይፋ አስጀምረዋል።
ኢትዮጵያ የእናንተን በሰላም ማደግ በእውቀት መታነጽ በጉጉት የምትጠብቅ እና ለዚህም ጥረት የምታደርግ ሀገር መሆኗን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል ።ተማሪዎችም በአዲስ ምዕራፍ ትምህርታቸውን ተከታትለው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባችኃል ያሉት ከንቲባ አዳነት አቤቤ መምህራን እና የትምህርት ዘርፍ አመራሮች የትምህርት ለጥራት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በ2014 የትምህርት ዘመን ከ910ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ አካሂደው ፤በዛሬው እለት በይፋ ትምህርት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል ።በትምህርት ዘመኑም በከተማዋ ለሚገኙ ከ600ሺህ በላይ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ምገባን ጨምሮ የትምህርት ግብዓት ቁሳቁስ መርሐግብር እንደሚከናወን ኃላፊው ተናግረዋል ።
በዕለቱም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የትምህርት ቁሳቁስ ለተማሪዎች ያስረከቡ ሲሆን የተማሪዎች ምገባ መርሃግብርን በይፋ አስጀምረዋል።