የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ የአዳማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጀልዴ እንዲሁም የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 23 -26 ለሚካሄደው የAfrican Mayoral Leadership Initiative (AMALI) City Leadership Forum ላይ ለመሳተፍ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ ተገኝተዋል።
ልዕኩ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኋላፊዎች እና በኬፕታውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በፎረሙ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ከተለያዩ የአህጉሪቷ የከተማ ከንቲባዎች ጋር ልምድ ለመለዋወጥንና ለመማማር መሆኑን በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃውን አድርሶናል፡፡