በዚሁ የልምድ ልውውጥ ላይ የአፍሪካ ከተሞችና ከንቲባዎች ከህዝብ ፍላጎት በመነጨ ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረጉ ረጅምና ትውልድ የሚሻገሩ ዘላቂ አሻራን እያሳረፉ መሄድ የለውጥ አዙሪትን የሚያፋጥኑ ትላልቅ ትልሞችም መተለም እንደሚጠበቅባቸውና ከተሞቻቸውን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ በማድረግ ለውጥን እያስመዘገቡ ህዝባቸውን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው አውስተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ተሞክሮ ቀርቧል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዘዳንት ዶ/ር አኪኑሚ ኤ.አዴንስያ በመድረኩ ለአፍሪካ ከንቲባዎች ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ ልማት ባንክ ከተሞችን ለነዋሪቻቸው ምቹ ለማድረግ እንዲያስችል ፤ ቀጥታ ለከተሞች ብድር ወይንም ፈንድ ማቅረብ እንደሚጀምር በዚሁ ወቅት ማብሰራቸው ለከተሞች ትልቅ እድል መሆኑ ተገልጿል ፡፡