ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሚድያው ለትውልድ ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ለመደገፍ ያስችል ዘንድ ተቋሙ እያስገነባቸው ካሉ እስቱድዮዎች የሕፃናትን ስቱድዮ ለማስገንባት እና በቀጣይም በጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የጎበኘነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት /EBC/ የሰራው ስራ ለከተማችን አዲስ እና ተጨማሪ ውበት ሊጨምር የሚችል እንደ ብሔራዊ ሚድያ ደግሞ ኢትዮጵያን በደንብ ከፍ ሊያደርግ የሚችል እና የሚመጥን ሚድያ እየሆነ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በንግግራቸው ላይ አክለውም ከትውልድ ግንባታ አንፃር በሚድያው ተፅኖ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በሚድያው ተጠቅመን ለትውልድ ግንባታ ስራው ብዙ ትውልድን መድረስ ይቻላል ዘንድ አዲስ የሕፃናት ስቱድዮ በሚል የሰየመውን ግንባታ መደገፍ ተገቢ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለስ ዓለም በበኩላቸው ሚዲያው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራችንን ገጽታ ለመገንባትት በሚያስችለው መልኩ እየተገነባ የሚገኝ መሆኑን አይተናል ያሉት ለከተማችን የቱሪዝም ዕድገት የበኩሉን አሻራ ማኖር የሚችልም መሆኑን ተዟዙረን ተመልክተናል ብለዋል ።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው በግቢው ውስጥ እያስገነባ ያለው ኢንፈራ እስትራክቸር ዕድሜውን የሚመጥንና ለኢትዮጵያ ሕዝብም የሚገባው ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
የኢቢሲ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ፍስሀ ይታገሱ ሚዳያው ከፖንአፍሪካኒዝም ታሪክ ጋር በማስተሳሰር የኢትዮጵያን ገፅታ በማስተዋወቅ የተሻለ ለመስራት ግብ ጥሎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል
በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ህንፃ ያሰበውን እንዲያሰካ የተቋማት ጉብኝትና ድጋፍ ተጨማሪ አቅም ነው ብለዋል።አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው ስራ ከግብ እንዲደርስ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።