“ለአዲስ ምዕራፍ ተልዕኮ ዝግጁ ነን” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የውይይት መድረክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በቅርቡ የተሾሙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ።
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝባችን ታገለግሉኛላችሁ ብሎ ድምጹን ብቻ ሳይሆን ተስፋም ጭምር ጥሎብናል ብለዋል።
በአዲስ ምዕራፍ በተነሳሽነት እና በቆራጥነት ህዝባችን የማገልገል ዕድል አግኝተናል፤ ማገልገል ደግሞ ከክብር በላይ ክብር ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
በለውጥ ሂደት በርካታ ሳንካዎች አሉ ፤እነዚህን ሳንካዎች በጥንቃቄ በማለፍ ህዝብ የጣለብንን ሀላፊነት ለመወጣት ሁሉም አመራር በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ መስራት እንደሚገባው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
“የ6ኛው ክልላዊ እና ሀገራዊ ምርጫ አፈጻጸም ስኬቶች እና ተግዳሮቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ” በሚል በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ሙሁራን የተደረገ ዳሰሳዊ ጥናት ላይ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።