በዚሁ መሰረት 12 ሆስፒታሎች በጋራ የጤና መንደር ለመገንባት ባቀረቡት የመሬት ጥያቄ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ካቢኔው ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ፓርቲ የተውጣጡ አባላቱን በማሳተፍ የጋራ ውሳኔ ማስተላለፍ ላይ የሄደበት ርቀትና እየገነባ ያለው አዲስ የዲሞክራሲ ባህል በጥንካሬ የተወሰደ ሲሆን ፤ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስና ለችግሮቹም ተመጣጣኝ መፍትሔ ለመስጠት የሄደበት የጋራ አመራር አሰጣጥና የማስፈፀም አቅም ትልቅ እርምጃ መሆኑ በጥንካሬ ተገምግሟል፡፡
በ2015 በጀት ዓመት የሥራ ሂደቱ የአሰራር ስርዓትን እና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽሉ እና የከተማ ስራን የሚያሳልጡ ፣ በከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ 181 ስትራቴጂክ የሆኑ ችግር ፈቺ ውሳኔዎችን በማሳለፉ የከተማዋን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ያሳለፏቸው ውሳኔዎችና ከውሳኔዎቹ 145ቱ በተሟላ ሁኔታ መፈፀማቸው በውጤታማነት ገምግሟል።
በካቢኔው ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል በማሳያነትም የ5 አዋጆችን እና የ19 የደንቦችን ባጠቃላይ 24 የህግ ስነዶችን ማፅደቅ መቻሉ ተመልክቷል።
በከተማዋ የመሬት አቅርቦት ፣ ለተለያዩ የከተማዋ መሰረታዊ ፍላጎት የበጀት ድጎማ ፤ የስራ እድል የመፍጠር ፣ የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ በየወቅቱ ለሚነሱ ማህበራዊ ጥያቄዎች ልዩ ውሳኔ እንደ ባህሪያቸው መደረጋቸው ለውጤታማነቱ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
ለአብነትም የመሬት ውሳኔ ካገኙት ፕሮጀክቶች መካከልም የአውሮፕላን መገጣጠሚያ ፤ የአቪየሽን እና ስፔስ ሙዚየም ፤ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፤ ኮንስትራክሽን ግብአት ማምረቻ ፕላንት ፤ የመድሀኒት ፋብሪካ ፤ የአልሙኒየም እና ብረታ ብረት ፋብሪካ ፣ የሆቴል ፣ የጤና ፣ የትምህርት ፣ የገበያ ማዕከላት የከተማዋን ኢኰኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት ታሰቦ የተወሰነ መሆኑን እና ውሳኔውም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል፡፡
በሌላ በኩል የካቢኔው ውሳኔዎችን በተገቢው ፍጥነት ያለ መተግበር ፤ የተሰሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ለህብተሰቡ ያለማሳወቅ መረጃ ለህብረተሰቡ በወቅቱ ያለ ማድረስ ችግሮች በቀጣዩ የበጀት ዓመት እንዲታረሙ በአፅንኦት አሳስቧል።
በመጨረሻም በ 2ዐ16 ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጠናከር ድክመቶችን በማረም ፣ የተሻለ የጋራ አመራር የመስጠት፣ ብቃት ማሳደግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።