የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የለውጥ አመራሩ ዘረፋና ሌብነትን ለመታገል በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪውን ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት: በገለልተኛ አካል እና በተጨባጭ ጥናት ላይ በመመርኮዝ ማጣራቱ ይታወቃል፡፡የተደረገውን ጥናት ግኝት መነሻ በማድረግ መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይተዋል፡፡

  1. በጥናቱየተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች የከተማ አስተዳደሩ እንዲወርስ እና በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ገቢው ለህዝብ ልማት እንዲውል፤
  2. በህገወጥመንገድ የተያዙ : ባዶና ዝግ ሆነው የተቀመጡ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤
  3. የቀበሌመኖርያ ቤቶችን አስመልክቶ በህገወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ የከተማው ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤
  4. የቀበሌየንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ቤቶች አስለቅቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንዲሰጥ ተወስኖአል፡፡
  5. ይህእስኪከናወን ታግደው ባሉበት እንዲቆዩ ለፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ውሳኔውን ማሳወቅ እንዳለባቸው፤ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግር እና ስርዓት አልበኝነት ከለውጡ በፊት ከ1997 ጀምሮ የተፈፀመ በመሆኑ ወደፊት እንዳይደገም በፅናት እንደሚሰራ እና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የተላለፈውን ውሳኔ የከተማው አቃቢ ህግ እየተከታተለ ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኖአል፡፡