የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንዳስታወቁት በ2014 በጀት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት 11.5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 13.7 ቢሊየን ብር ወይም የእቅዱን 118 % መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል ።
አፈጻጸሙም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ3.5 ቢሊየን ወይም የ37% ብልጫ እንዳለው አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል ።
ይህንን ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው በቢሮው ከአሰራር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተለይ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ያለ እንግልት ባሉበት ሆነው መስተናገድ የሚያስችል የኢቲ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በመዋሉ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የታክስ ህግን በሚጥሱት ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ሃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
በቀጣይም የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉና ከዚህ በፊት ያልከፈሉ የደረጃ ለ እና ሐ ግብር ከፋዮችም ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር ቅጣትና ወለዱም በዛው ልክ እየጨመረ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲከፍሉ አቶ ሙሉጌታ ጥሪ አቅርበዋል።