የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ውሃ እና ፍሳሽ ባለጣልን በከተማችን ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋራ ተያይዞ የሚስተዋለውን የውሃ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል ፡፡
በዘንድሮ በጀት ዓመት ከፕሮጀክቶች ግንባታ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ ከገጸ ምድር የውሃ መገኛዎች 74.46 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ እንዲሁም ከከርሰ ምድር የውሃ መገኛዎች 165.46 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማልማት ለነዋሪዎች ተደራሽ ለማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴመጀመሩን ገልጧል ፡፡
ባለፉት ሶስት ወራትም ከገጸ-ምድር እና ከከርሰ ምድር የውሃ መሰረተ ልማቶች 46.84 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ አምርቶ አሰራጭቷል፡፡
አዲስ የውሃ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነት ያክል በጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶች፣ ለሪል ስቴትና ለግሰብ መኖሪያ ግንባታዎች 52.036 ደንበኞች ብሎም ህጋዊ ሰነድ ለሚያቀርቡ ለ12,193 መደበኛ ደንበኞች በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች አማካኝነት የውሃ ቅጥያ አገልግሎት ለመፈጸም የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን ማጠናቀቁን ባለስልጣኑ አክሎ አስታውቋል ።