*********************
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በአማራ፣ በአፋርና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰቡን አስታወቀ።
ለተፈናቃዮች ያሰባሰበውን ሃብት የሽኝት መርሀግብር አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወይዘሮ የሺ ወልዴ እንደገለፁት፣ ሃብቱ የተሰባሰበው 200 ለእናቴ አንድ ዕቃ ለአንድ ተፈናቃይ በሚል ሲሆን፤ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በተጀመረው ንቅናቄ በዓይነት ብቻ ሃያ ሚሊየንና በጥሬ ገንዘብ 3 ነጥብ 1 ሚለየን ብር ገቢ ተደርጓል፡፡
ሊጉ ለሦስቱ ክልሎች ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ችሏል። የተሰበሰበው ሃብት አሻባሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ወገኖቻችን ለፍተው ካቀኑት ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው ብለዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ከተለያዩ በጎ አድራጓት ተቋማትና ግለሰቦችን በማስተባበር በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተመላክቷል።