የአዲሰ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሰንቀሌ በሚገኘው የኦሮሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ለተከታታይ 5 ወራት ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 100 መደበኛ ፖሊሶችን በዛሬው እለት አስመርቋል ፡፡በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውም ለተመራቂ ፖሊሶች የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው የምርቃት ፕሮግራም መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ 3ሺህ 100 ምልምል ፖሊሶች 617ቱ ሴቶች ሲሆኑ የአካል ብቃት፣ በአድማ ብተና እንዲሁም ወታደራዊ ሰልፍና ወንጀል ምርመራ ስልጠና ወስደዋል ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፖሊሳዊ አካዳሚ ከሶስት ሳምንት በፊት በ22ኛ እና 23ኛ ዙር ስልጠናቸውን 1516 ምልምል ፖሊሶች ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አስመርቆ ወደ ስራ ማስገባቱ የሚታወስ ነው።