የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጋርነት ከሚያስገነባቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል፣ የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ዋንኛው መሆኑን አቶ አዲስ አረጋይ የአዲስ አበባ ከተማ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተናግረዋል።
ግንባታውም ከነበረበት ችግር በማላቀቅ የመጀመሪውን የግንባታ ምዕራፍ አጠናቆ ለማስረከብ አስፈላጊው ድጋፍ በመደረግ ላይ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በመያዝ እያስገነባ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዳይሬከተሩ፣ የፕሮጀክቶች ግንባታ በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ በማድረግ ረገድ፣ በትኩረት እንደሚሰራ ነው የገለፁት።
አሁንም የተጠናቀቁና ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ፤ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ እንዲሁም በቀጣይ አመት የሚጀመሩ አዳዲስ ግንባታዎች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ፤ በትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤቱ አማካይነት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ በመመደብ እየደገፈ፤ ከጊዜና ከአላስፈላጊ የገንዘብ ወጪ ለመዳን እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋ