የአድዋ በአል ያስጨፍራል እንጂ !! በአድዋ ያልተሳተፈ ሰው የለ ፡ ምንድን ነው ሽምያው አሁን በጋራ ሆነን የማናከብረው ?
ምንድን ነው ፀብ የሚያመጣው ነገር? ታሪክ መማርያ እንጂ የምኒልክን የባልቻን ገድል እየዘከርክ ገድል ሳትሰራ ታሪክ ሳትሰራ ከምታልፍ ከዛ ተምረህ የራስህን ታሪክ ሰርተህ መቀጠል ነው።
ከኛ ኋላ ቀር እሳቤ የሚመጣ እንጂ አድዋ ወደፊት ማሰብ ያለብን በየክልሉ በየከተማው የብሄር ብሄረሰቦች ዘፈን እየዘፈንን ኢትዮጵያዊ ነፃነታችንን በጋራ የምናሞቀው የምናደምቀው እንጂ የምንጣላበት አይደለም። እኛ ነን እንጂ የምንጣላው እነሱ እኮ አብረው ነው የሞቱት።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ