ቀደም ሲል የመዋቅር (structure) ግንባታ ስራው የተጠናቀቀው የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት ግንባታ አሁን ላይ የተለያየ የማጠቃለያ ስራዎች እየተከናወኑለት መሆኑ ተገልጽዋል፡፡
በአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት ተወካይ መሃንዲስ ፈለቀ ወ/ዮሃንስ (ኢንጅነር) እንደገለፁት የመዋቅር (structure) ግንባታ ስራው መጠናቀቅን ተከትሎ የማጠቃለያ ስራዎች(Finishing works) የሆኑት የአሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣የውሃ መስመር ዝርጋታ፣የተለያዩ የወለል ንጣፍ ስራዎች (ሴራሚክ ስራ)፣የጅብሰም እና ሌሎች መሰል የማጠቃለያ ተግባራት በህንጻው ውስጣዊ ክፍሎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለሙያው አክለውም አጠቃላይ ሙዚየሙን ለአገልግሎት ለማብቃት የማጣቃለያ ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች ስራዎች እየተፋጠኑ ሲሆን፣ በፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም ደረጃ ከ77 ከመቶ በላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡
ይህ ዘመን ተሻጋሪ የግንባታ አሻራ መዲናችን አዲስ አበባ የእንቅስቃሴዎች ማእከል መሆኗን ከማመላከቱ በሻገር፤ሁሉም ኢትዮጲያዊያን ከያሉበት ተሰባስበው ለድል የተነሱበትና ድል ያስመዘገቡበት ታላቅ ማስታወሻ ነው፡፡