ጳጉሜን በመደመር በሚል ሃሳብ ከተከበረው ከመጀመሪያው የበጎ ፈቃድ ቀን አንስቶ ጽዳት በከተማችን አዲስ አበባ ባህል ሆኑ ይቀጥል ዘንድ ለማስቻል በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ከነዎሪዎች ጋር በጋራ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች ጽደት እያደረጉ ይገኛሉ።
ከተማ አስተዳደሩ ከለውጡ ማግስት አንስቶ የአረንጓዴ አሻራ፣ የከተማ ጽዳትና ማስዋብ ፣የቱሪዝም መዳራሻዎች ግንባታ፣የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የቅዳሜና እሁድ ገበያን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የማዕድ ማጋራት ፣ለአቅም ደካማ ወገኖች የቤት ዕድሳትና ግንባታን ተከናውኗል።
ከተማችን የሁሉም ቤት የሆነች ውብ አዲስ አበባን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገች እንደምትገኝ ይታወቃል ።
የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተከናወነው የጽዳት መረሃ-ግብር ላይ የተሳተፉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሁሉም የከተማችን ነዋሪ በየዕለቱ የሚኖርበትን አካባቢ ማጽዳት ቢችል ውብ አዲስ አበባን በሚፈለገው ደረጃ መገንባት ይቻላል ብለዋል ።
በጽዳት መረሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ለሚኖሩ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የማዕድ ማጋራት አድርገዋል ።