– የተቋም ግንባታ በተመለከተ የተቋማት ሪፎርም በማካሄድ ፤ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት አሰጣጥ በተመረጡ ተቋማት በመተግበር እና የአመራርና የፈፃሚውን ተቋማዊ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም የመገንባት ስራ ተሰርቷል፡፡
– በክፍለከተማ እና በወረዳዎች ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል
– 21 ወረዳዎችን ስማርት የማድረግ በ9ዐ ቀናት የከተማው ልዩ እቅድ ሆኖ ተከናውኗል:: በተጨማሪም ለ 11 ወረዳዎች ምቹ አገልግሎት መስጫ የህንፃ ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡
– ገቢ አሰባሰብ ለማሻሻል የE-tax ፤ የE-filing እና የSIGTAS፣ የቴሌብር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ አሳውቀው መክፈል እንዲችሉ ተደርጓል
– የንግድ ፍቃድ እድሳትና የጤና ዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎትን በማስፋትና በማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ በከተማ አስተዳደሩ 7 ሆስፒታሎችና በ11 ጤና ጣቢያዎች ተግባራዊ ተደርጎ ወረቀት ማስቀረት የሚያስችል ስራ ተጀምሯል
– በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ አስፈጻሚ ተቋማት የሚሰጧቸውን የተመረጡ አገልግሎቶች ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍና የመንግስት የስራ ሰዓትን በማሻሻል የከተማውን የአገልግሎት አሰጣጥ በአዳዲስ አስተሳሰብና አሰራሮች እየተኩ መሄድ የሚያስችል ዝርዝር ጥናት እና የሕግ ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንገኛለን
– የሰራተኞች እና ተገልጋዮች እርካታ ደረጃ በማጥናት እና በግኝቶቹ መሰረት የማስተካከያ እና የእርምት እርምጃዎች በመውሰድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ ነው፡፡
– በሚሊዮን የሚቆጠሩ የከተማችንን ነዋሪዎች አወያይተን፣ አስተያየታቸውን አድምጠን፣ ጥያቄና ቅሬታቸውን ተቀብለን በማጣራት ለነዋሪው ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡