የኢሬቻ በዓል አከባበር በመላው አዲስ አበባ ከዛሬው እለት ጀምሮ ከመስከረም 18 እስከ መስከረም 21 ድረስ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡
• በዛሬው እለት በመላው አዲስ አበባ የፓናል ውይይቶችና ኤግዚቢሽኖች የተከፈቱ ሲሆን
• በነገው እለት መስከረም 19 ደግሞ በክ/ከተማ ደረጃ የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡
• መስከረም 20 በማእከል ደረጃ ከኦሮምያ ክልል ጋር በመቀናጀት የማጠቃለያ የፓናል ውይይት ይካሄዳል
• በ21 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር በአባገዳዎች ብቻ እየተመራ ይካሄዳል፡፡
ኢሬቻ የወንድማማችነት/እህትማማችነትና የምስጋና በዓል ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ የጨለማውን ጊዜ አሳልፈን ብራን ያሳየኸን ፈጣሪ እናመሰግናለን!! መሬቱን አረጠብክልን ፤ውሃው ሞላ ፤የደፈረሰው ጠራልን እናመሰግናለን! በማለት ለፈጣሪው ምስጋናውን የሚያቀርብበት ድንቅ በዓል ነው፡፡