የግብፅን አቻውን 2 ለምንም በመርታት ታላቅ ጀግንነት የፈፀመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርስ በባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እንዲሁም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ሠራተኞች አቀባበል ተደርጎለታል።
ክቡር ሚኒስቴሩ ለልዑክ ቡድኑ የአበባ ጉንጉን በማበርከት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።