“ሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋን በየፈርጁ መታደሏን ከሚያሳዩን ሥፍራዎች አንዱ የጎፋ ዞን ነው። ከዞኑ አልፎ ክልሉን ለማልማት የሚያስችል ያልተነካ ዐቅም አለው። ባለ ግርማ ሞገሱ ወይላ ተራራም በውስጡ የያዘው ብዝኃነት የሀገራችን የኢትዮጵያ ማሳያ ያደርገዋል። የዶጫ ደምበላ አርሶ አደሮች በ80 ሄክታር ላይ ያመረቱት ሰሊጥ፣ ማሾ፣ አኩሪ አተር፣ ጤፍ እና ፍራፍሬም አካባቢው የተፈጥሮ በረከት እንደተቸረው የሚያሳዩ ናቸው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ