በ2014 በጀት ዓመት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲኘሎማሲያዊ ዘርፎች ከዕቅዱ አኳያ ተስፋ ሰጪ ውጤት ያተገኙበት ቢሆንም፣ ግጭትና መፈናቀል ያልተሻገርናቸው ችግሮች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን ጦርነት እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች በንፁሐን ዜጐች ላይ የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ በአሉታዊ ጎናቸው የሚታወሱ ብቻ ሣይሆኑ የበርካቶችን ልብ የሰበረ መሆኑንም ገልፀዋል።
መንግስት ግጭት ጨርሶ እንዲያበቃ ከማንኛውም ወገን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደርና ልዩነቶችን በሠላምና በውይይት ለመፍታት ሀሳብ ማቅረቡን ክብርት ሣህለወርቅ አስታውሰው ይህንን ዕድል ስለ ትግራይ ሕዝብ ሲል ህወሃትም የሠላም ጥሪውን በመቀበል ለድርድር እንዲቀመጥ የቀረበውን ጥሪ ማክበር እንደሚገባው አሣስበዋል፡፡
መንግስት ማንኛውንም አይነት ልዩነቶችን በመነጋገር መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በማመን ያለቅድመ ሁኔታ ለመወያየት አሁንም ጥሪውን ያቀርባልም ብለዋል፡፡
Hopr parliament