ወጣቶቹ 18 እና 19 ዓመታቸው ሲሆን፤ ያገለገሉ ፕላስቲኮችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለመልቀም ወንዝ ዉስጥ ገብተው እንደነበር የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልጸዋል።
አደጋው የተከሰተው በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እሪ በከንቱ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ መሆኑም ታውቋል።
ወጣቶቹ ለ25 ደቂቃ ያህል ከጎርፉ ጋር ሲታገሉ መቆየታቸውንም አቶ ንጋቱ ገልፀዋል።
በመሆኑም በከተማችን የተለያዩ ወንዞች ዉስጥ በመግባት ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በመሰብሰብና በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በዚህ በክረምት ጊዜ በወንዝ አካባቢ ያለ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ አቶ ንጋቱ ምክራቸውን ለግሰዋል ።
በተመሳሳይ ታዳጊዎችና ህጻናት ጎርፍ ያመጣቸዉን ቁሳቁሶች ለማዉጣት ወንዝ ዉስጥ ለመግባት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም እንዲያቆሙና ወላጆችም ልጆቻቸዉን መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ባሳለፍነው እሁድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ጎርፍ ያመጣዉን ኳስ ለማዉጣት በወንዝ ዉስጥ የገቡ የ9 እና የ14 አመት ታዳጊዎች ህይወታቸዉ ማለፉ ይታወሳል ።