የከተማችን ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንና ለታላቁ የህዳሴ ግድባችን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ::
“የእናት ሆድ ዥንጉርጉር” እንዲሉ ኢትዮጵያ ከጀርባዋ የሚያጠቋት እና ለባዕዳን አሳልፈው የሚሰጧት የጥቂት ባንዳዎች እና የእናት ጡት ነካሾች ብቻ ሳትሆን ሚሊዮኖች “ከአገሬ በፊት እኔ ልቅደም” ብለዉ ከፊት የሚሰለፉላት ልጆች ያላት አገር ናት ።
የዛሬው መድረክ ዳግም ይህንን እዉነት ያሳየ ነበር። በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ለጀግናው እና የኩራታችን ምንጭ ለሆነዉ የመከላከያ ሰራዊታችን ለማሰባሰብ ተግባብተናል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበአል ሹመታቸው ዕለት ባደረጉት ንግግር እንዳሉት “ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም ናት። ኢትዮጵያ በየመስኩ የሚዋደቁላት፣ ክብር የሚሰጧት ጀግኖች ልጆች ያሏት አገር ናት”። የትላንት ምሽት የፀጥታው ምክርቤት አቋም እና የዛሬው መድረክም ይህንን እዉነት ዳግም ያረጋገጠ ነዉ።
ክብር ለኢትዮጵያ ሰላምና ሉአላዊነት መከበር መስዋዕት እየከፈሉ ላሉ ለጀግናው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት !!
ክብር ለኢትዮጵያ ሀቀኛ ልጆች!!