የከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪ ከሆኑ ምሁራን ፣ የሚድያ ባለሙያዎች ፣ የእምነት አባቶች ፣ ታዋቂ ሰዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር በከተማችን ያለፉት 15 ወራት የእቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች ብሎም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
መዲናችን የጋራችንና የሁላችን እንደመሆኗ መጠንቀቅ ሁሉም ሀላፊነት የሚሰማው ዜጋ ስለ እድገቷና ቀጣይ ስራዎች ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ በሀሳብም በጉልበትም በገንዘብም ሊያበረክት ይገባል።
አዲስ አበባን በመመካከር ፣በመተባበር ፣በመደማመጥ እና በሰለጠነ የሀሳብ ልዕልና ሰላማዊ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንደ ስሟ አበባ ማድረጋችንን እንቀጥላለን።”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ