በስፖርት ማዘውተርያ ቦታዎች፣ በስራ እድል ፈጠራና በመልካም አስተዳደር ዙርያ ወጣቶቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ወስደን የሚታረመውን አርመን፤ የሚስተካከለውን አስተካክለን በጋራ ለመፍትሄው እንደምንረባረብ ላረጋግጥችሁ እወዳለሁ!!
የአዲስ አበባ ወጣቶች ሃሳባቸውን በሰለጠነና በሰከነ መንገድ የሚያንፀባርቁ እንጂ በአመፅ ወይንም የሌላ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደማይፈልጉ አረጋግጠዋል፡፡
ከሌሎች የከተማችን ወጣቶች ጋር ተከታታይ መድረኮችንና ውይይቶችን ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
የአዲስ አበባ ወጣቶች የከተማችን የሰላምና የለውጥ ተምሳሌት ሆነው ይቀጥላሉ!!
ወጣቶች ላበረከታችሁልኝ ስጦታ አመሰግናለሁ ፤ መጪው ግዜ ብሩህ ነው!!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ