“ሁለንተናዊ የተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለከተማችን ዘላቂ ሰላም” በሚል የከተማ አስተዳደሩ ከፍቸኛ አመራሮች ከተለያዩ ክፍለከተሞች ከተውጣጡ ነዋሪዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተካሂዷል ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ እና የሲቪክ ማሕበራት ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ባዩ ሽጉጤ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን በተመለከተ ለነዋሪዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
የከተማችን ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ እና ሀገር ለማፍረስ የሚጥሩ አካላትን ሴራ መክሸፍ እንደሚገባ አቶ ጥራቱ በየነ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።
በውይይቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች በበኩላቸው የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ እና የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ እየሰሩ ያሉ አካላትን ለማጋለጥ እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ሕልውና ለማስቀጠል እያደረገ ያለውን ዘመቻ በተባበረ ክንድ እንደሚደግፉ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።