የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ በተካሄደው ትግል የተገኙ አንፀባራቂ ድሎችን ለማስቀጠል እና በድህረ ጦርነት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድም መፍታት ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
ዉይይቱ ከዛሬ ጀምሮ ለመጪዎቹ 3 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን መሰል የውይይት መድረኮች በቀጣይም በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ መዋቅሮች እና በነዋሪው ህዝብ ደረጃ ጭምር የሚካሄድ ይሆናል ፡፡
አገርህን በዘላቂነት አልማ!
የፈረሰዉን አብልጠን እንገንባ !
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ !