የከተማ አስተዳደሩ ለ2013 በያዝነው እቅድ መሰረት አንድ ሺህ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እና ለአገልግሎት ማብቃት ችለናል። ይህ በከተማችን ያለውን የስራ አፈጻጸምን ልምድ በሁለት እጥፍ አሳድጓል። ዛሬም ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቱሉ ጉዶ ፕሮጀክት በቀን 68ሺህ ሜትር ክዩብ መስጠት የሚችል የንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መርቀናል። ይህ ፕሮጀክት ያለበትን አካባቢ ጨምሮ በአቃቂ ቃሊቲ ፣ ቦሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ እና ቂርቆስ ክ/ከተሞች የንጹህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪም 22 ሺህ ሜትር ክዩብ በቀን መስጠት የሚችሉ የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን በአጠቃላይ ለ2013 በያዝነው እቅድ መሰረት በቀን 90 ሜትር ክዩብ ለአገልግሎት በማብቃት የይቻላልን መንፈስ ያሳደርንበት መሆን ችልዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶችም የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃ የማምረት አቅሙን ከ 574ሺህ ወደ 664 ሜትር ክዩብ በማሳደግ ተችሏል።