ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች የግብርና ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ለህዝብ እናቀርባለን ባሉት መሰረት ኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ጋር በመተባበር የጤፍ ምርት ለነዋሪዎች እየቀረበ መሆኑ ይታወቃል።
በተፈጠረው የገበያ ትስስር በዛሬው ዕለት ከአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የጤፍ ምርት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መቅረብ የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ምርት በዘላቂነት ወደ ከተማዋ የሚገባ ይሆናል:: ዛሬ የገባው የጤፍ ምርት በከተማዋ ውስጥ ባሉ ሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት በኩል ለሁሉም ክፍለከተሞች የሚከፋፈል ሲሆን ህብረተሰቡ ወደእነዚህ ማዕከላት በመሄድ መሸመት የሚችል መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን::