የከተማ አስተዳደራችን በተለያዩ አካባቢዎች በ 2.78 ቢሊዮን ብር እየገነባቸው ካሉ 6 ዘመናዊ የመሸጋገርያ ድልድዮች መሃከል የኢምፔርያል ተሻጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ጉብኝተናል።
ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው ቀድሞ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ እና ለከተማዋም አድገት የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ይደረጋል፡፡
አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና አበባ የማድረግ ጉዟችን በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡