“የዘንድሮ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል።
የከተማችን ህዝብ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ላሳየው አስተዋይነት የተሞላው በሳል እንቅስቃሴ አድናቆቴንና አክብሮቴን መግለፅ እፈልጋለሁ።
እኛም በጎንደር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ስለተደረገልን ደማቅ አቀባበል የክልሉን ፣ የከተማውን አመራሮችና ነዋሪዎችን ከልብ አመስግናለሁ ።
ይህ ለከተማችን አዲስ አበባም ይሁን ለመላው ኢትዮጵያ ድምቀትና ሃብት የሆነ በዓል፣ ምዕመኑ በነቂስ ወጥቶ ተሳትፎበት በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የላቀ አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ የእምነት አባቶቻችን፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ የከተማችን ወጣቶች፣ በየደረጃው ለምትገኙ አመራሮችና መላው የከተማችን ነዋሪዎች ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።
ፈጣሪያችን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ