በትናንትናው እለት በዚሁ ቦታ የፍሳሽ ቦዮች በግንባታ ተረፈ ምርት በመደፈናቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ገንፍሎ የወጣ ጎርፍ በመጋዘን ቤት ውስጥ ተጠራቅሞ የመጋዘኑን አንዱን የግንብ ግድግዳ በመናድ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።
በዛሬው እለት ጉዳቱ የደረሰበትን ቦታ በአካል ተገኝተው የጎበኙትና ጉዳት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች ያፅናኑት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ዝናቡ ተጠናክሮ መቀጠሉን ግምት ውስጥ በማስገባት ጎርፉ ቀጣይ ጉዳት እንዳያስከትል የተጀመሩ የመፍትሄ እርምጃዎች በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደርጉ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰለሞን ፍስሃ በበኩላቸው በትናንትናው እለት በስምንት ቤቶች የሚኖሩ 30 ቤተሰቦች ላይ ጉዳት በማድረስ ለሁለት ሰዎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት የሆነው የጎርፍ አደጋ በድንገተኛ የጣለው ከአቅም በላይ የሆነ ዝናብ የፍሳሽ ቦዮችን በመዝጋቱ የተከሰተ እንደሆነ ገልፀዋል፤ ቦታው ቀደም ሲል በስጋትነት ከተለዩት አካባቢዎች ውስጥ የተካተተ እንዳልነበረም ጠቁመዋል።
የአዲስ አቡባ መንገዶች ባለስልጣን የተደፈኑ የፍሳሽ ቱቦዎች ጠረጋ ስራ ሰማከናወን በተጨማሪ የማሺነሪ አቅርቦትን በመጨመር አፋጣኝ ጉዳቱን የመቀነሰ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ ተናግረዋል ።
በአዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ክረምቱ እየያለ በመምጣቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢውን የመከላከል ተግባር እንዲያከናውኑ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚሁ ወቅት ጥሪ ቀርቧል።
+3
Toosh Tarree Page, Wolde Abera and 533 others
16 Comments
45 Shares
Like
Comment
Share