(ዜና ፓርላማ)፤ ጥቅምት 8፣ 2015 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30፣ 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብስባው ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን ባደመጠበት ወቅት ነው፡፡
የድጋፍ ሞሽኑ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተደርጎበት የሚጸድቅ ሲሆን የውይይት የሚደረግበት ጊዜ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል፡፡
የምከር ቤቱ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡