የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አመት በገባ በ1 ሳምንት ውስጥ ያሰባሰባቸውን የአይነት ድጋፎች በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የአዲስ አበባ የከተማ መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፤የሰራዊቱ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት የስንቅና የቁሳቁስ ድጋፍ ርክክብ አድርጓል፡፡
ወ/ሮ ነጂባ አክመል የፋይናስ ቢሮ ኃላፊና የከተማ አቀፍ የሌጀስቲክ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደተናገሩት የከተማችን ሕዝብ ለሀገር መከላኪያ ሰራዊት እያሳየ ያለውን ደጀንነት እኛም እንደ ከተማ አስተዳደር ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን በዚህም መተሳሰባችንን በብዙ መንገድ እያሳየን እንገኛለን ብለዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር የበጀትና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል አብዱልሰመድ ኢብራሂም ሀገርን ለማፍረስና ለመበተን የተቃጣብንን አደጋ ለመቀልበስ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ይመለከተዋል ያሉ ሲሆን እየተደረገ ላለው ድጋፍ በሰራዊቱ ስም አመስግነዋል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደርም 171 በሬ፣302 በጎች እንዲሁም ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ በጠቅላላው 14ሚሊየን 123 ሺህ 203 ብር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አበርክቷል፡፡