የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አንድ ግለሰብ በህገ ወጥ መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መድሃኒት በቦርሳ ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ለመሸጥ በመደራደር ላይ እያለ በትላንትናው ዕለት ነሃሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል ።
ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል 10 ብልቃጥ የቻይና ሲኖ ፋርም(sino pharm) እና 3 ብልቃጥ የአሜሪካ ጆን ኤንድ ጆንሰን (john and jonson) የተባሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት መድሀኒቶችን እንዲሁም የክትባቱ መስጫ 12 መርፌዎች እና 3 የማቀዝቀዣ ቁሶችን ግብይቱ ለመፈፀም ሲስማሙ ከነበሩ 3 ተጠርታሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡
ክትባቶቹ ከየት ተሰርቀው እንደወጡ ለማወቅ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ለገበያ የሚቀርቡ መድሀኒቶች በጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ከጤና ተቋማት እና ከህጋዊ መድሃኒት መሸጫ መደብሮች ውጪ ማንኛውንም መድሃኒት ገዝቶ ባለመጠቀም ጤናውን እንዲጠብቅ ፖሊስ አሳስቧል ።
ህብረተሰቡም እንዲህ አይነት ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት እ