“ዘንድሮ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 37% ደርሶ የነበረ ቢሆንም፤ ወደ 30% ዝቅ ለማድረግ ተችሏል። ነገር ግን ከዚህ የበለጠ ዝቅ ማድረግ አለብንም፤ እንሰራለንም። ምርታማነትን ለማስፋት ዘንድሮ 2ሚሊዮን ሄክታር ተጨማሪ መሬት ይታረሳል። በዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ15 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ይታረሳል ማለት ነው።
የኢትዮጵያ እዳ ለውጡ ሲመጣ 59% አካባቢ የነበር ሲሆን፣ አሁን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ 38% ለማድረስ ተችሏል። በብዙ ችግር ውስጥ ሆነንም፤ የወረስነው እዳ ቢሆንም እየከፈልን እንገኛለን። በሚቀጥለው ሶስት ዓመት ውስጥ ወደ 30% ለመቀነስ እንሥራለን።”