የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ እና የዓለምአቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ መንሱር ቢን ሙሳላም በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ መንግስት በትምህርት ልማት የሚያደረገውን ጥረት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚደርገውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ የዚህ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱ በአዲስአበባ መከፈቱ ትብብሩን ያሳድገዋል ብለዋል።
የደቡብ ደቡብ ትብብር አካል የሆነው ይህ ተቋማ በትምህርት ዘርፍ ያለውን አማራጭ አቅሞች ለመጠቀም እንደሚያስችል ገልፀዋል።
የዓለምአቀፉ የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ መንሱር ቢን ሙሳላም በህብረት የምንመኘው መጪው ጊዜ በትምህርት ብቻ ሊሳካ የሚችል ነው ያሉ ሲሆን ለዚህ ውጤትም በትብብር መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።