የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፋይዛ መሐመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ፤በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀንን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል ።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የቱሪዝሙን ዘርፍ ክፉኛ አዳክሞታል ያሉት ኃላፊዋ የበዓሉ መከበርም በዘርፉ የተዳከመውን ኢኮኖሚያዊ ለማነቃቃት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
“ቱሪዝም ለሁለተናዊ እድገት!” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የቱሪዝም ቀን በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን የማስጎብኘት ፣በልዩ ልዩ የጎዳና ላይ ትርዒቶች እና በስፖርት ቱሪዝም በመሳሰሉት ዝግጅቶች የኮቪድ19 ወረርሽኝ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ እንደሚከበርም ፋይዛ መሐመድ ተናግረዋል፡፡