የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ መስከረም 21 በሆረ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ደግሞ መስከረም 22 በሆራ ሀርሰዲ እንደሚከበር አባገዳዎች አስታውቀዋል፡፡
በዘንድሮው የኢሬቻ በአል አከባበር ዙሪያ አባገዳዎች በአዳማ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በበአሉ ላይ ሁሉም በአንድነት አጊጦ ተገኝቶ በሰላማዊ መንገድ በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉ የህዝቡ በመሆኑ የገዳ የሆነውን ባንዲራ ብቻ መያዝ እንዳለበትና ሌላ ባንዲራ መያዝ እንደማይቻል አባገዳዎች በመግለጫቸው አሳስበዋል።
በዓሉም የሰላም የአብሮነት የፍቅር የአንድነት እንዲሆን ተመኝተዋል።