መርሀ ግብሩ በርካታ የዳያስፖራ አባላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጀው የዳያስፖራ ፓርክ ውስጥ ተካሂጿል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አበቤ ትውልድ እንዲማርና ወቅቱን እንዲያስብ በማለም የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዳያስፖራው መታሠቢያ ይሆን ዘንድና አካባቢን ለማልማት ከተማ አስተዳደሩ የዳያስፖራ ፓርክ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የዲያስፖራ ፓርክ መሰየሙ ትርጉሙ ከአረንጓዴ ልማት በላይ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ የዳያስፖራው የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎም እንደሚያበረታታ ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ ዳያስፖራዎች የእናት አገር ጥሪን ተቀብለው አሻራ ለማኖር መብቃታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
በቀጣይም መሰል ተሳትፎዎችን በማጉላት አገርን በሁሉም መስክ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡